Blog Details

ኮርቴዞል/Cortisol

ኮርቴዞል/Cortisol

  በሰውነታችን ዉስጥ ለተከማቸ ስብ በተለይም ሆድ አካባቢ ለሚፈጠር ስብ ብዙ ምክንያቶች ቢኖሩም ዋነኛዉ ተጠያቂ የኮርቴዞል ሆርሞን ነው።ስለዚህ በዛሬው ቪዲዮአችን የዚህን ሆርሞን ምንነት እና እንዴት መቆጣጠር እንደሚገባን የምንመለከት ይሆናል አብራችሁን ቆዪ።

      ኮርቴዞል የስቴሮይድ ሆርሞን ሲሆን በሁለቱ የአድራናሊን ግላንዶች ውስጥ ይመረታል።በዋነኝነት ሰውነታችን ልዩ ጫና እና ጭንቀት ውስጥ በሚሆንበት ጊዜ ምርቱ የሚጨምር በመሆኑ stress hormone/የጫና እና የጭንቀት ሆርሞን በመባል ይታወቃል።ይህ ሆርሞን መጠኑ ከፍም ዝቅም ሲል ብዙ ጤናዊ መዘዞችን ቢያመጣም በትክክለኛው መጠን ግን ብዙ ጠቀሜታዎች አሉት እነዚህም :-

-ጫና;ጭንቀት እና አደጋን ሰውነታችን እንዲቋቋም

-የግሉኮስን ሜታቦሊዝም ይጨምራል

-የደም ግፊትን ለመቆጣጠር ይረዳል

-ብግነትን/inflammation /ለመቀነስ ይረዳል

 ሰውነታችን ዝቅተኛ ወይም ከፍተኛ ኮርቴዞል ካመነጨ ምን ይሆናል

                ከፍተኛ

-የክብደት መጨመር እና በሆድ እና በፊት አካባቢ ስብ እንዲከማች ያደርጋል

-ብጉር እና የተሰነጠቀ ቆዳ ይፈጥራል

-በሴቶች ላይ የፊት ፀጉር ማብቀል እና የወር አበባ መዛባት

                በጣም ሲያንስ

-ከፍተኛ ድካም

-ማቅለሽለሽ እና ማስመለስ

-የጡንቻ መድከም እና ክብደት መቀነስ

-የሆድ ህመም

        ከእነዚህ ጉዳቶች ለመጠበቅ እና ጤነኛ እና ሳቢ ሰውነት ለመገንባት ይሄንን ሆርሞን መቆጣጠር እጅግ በጣም አስፈላጊ ነው ለዚህ ደግሞ በዋነኝነት ጭንቀትን ማስወገድ ዋነኛ መፍትሔ ነው።ጭንቀትን እና ሰውነት ላይ የሚኖር ጫናን ለመቀነስ ደግሞ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን እጅግ በጣም ጠቃሚ ናቸው በተለይ ደግሞ አእምሮን ዘና እያደረጉ የሚሰሩ እንደ ዳንስ ፊትነስ አይነት ስራዎች ነገሮችን በጣም ቀለል እንደሚያደርጉ ብዙ ጥናቶች ያመለክታሉ።